ጣና ፍሎራ ኃ/የተ/የግ/ማህበር
በምስራቅ አፍሪካ እ.ኤ.አ በ2025 በትርፋማነቱ ግንባር ቀደም የአበባ ቢዝነስ ኩባንያ ሆኖ ማየት
ጋፋት ኢንዶውመንት በስሩ ካቋቋማቸውና በባለቤትነት ከሚያስተዳድራቸው ኩባንያዎች አንዱ ነው፡፡ጣና ፍሎራ፡፡ኩባንያው በዋነኛነት ከፍተኛ ጥራት ያለውን አበባ በማምረት በአለም አቀፍ ደረጃ ለተጠቃሚ ለማድረስ ግብ አድርጎ በ2000 ዓ.ም የተቋቋመ ኩባንያ ነው፡፡ የጣና ፍሎራ የእርሻ ቦታ ከባህርዳር ከተማ በስተሰሜን ምእራብ በ 17 ኪ.ሜ ርቀት ላይ በ124 ሄክታር መሬት ላይ ያረፈ ሲሆን ከዚህ ውስጥ 40 ሄክታሩ ለአበባ ማምረቻ ውሏል፡፡በአሁኑ ወቅትም የሚከተሉትን 20 የአበባ አይነቶችን በማምረት በዋነኝነት ለውጪ ገበያ በማቅረብ ላይ ይገኛል፡፡እነዚህም፡-
ተ.ቁ |
የአበባው አይነት |
1 |
Upper class |
2 |
Furiosa |
3 |
Burgundy |
4 |
Grand Europe |
5 |
Lovely Jewel |
6 |
Heidi |
7 |
Ace Pink |
8 |
Orchstra |
9 |
Elisa |
10 |
Mariyo |
11 |
Intense |
12 |
Moon Walk |
13 |
Good Times |
14 |
Belle Rose |
15 |
Out Low |
16 |
Catch |
17 |
La Belle |
18 |
Athena |
19 |
Bisou |
20 |
Aranico |
ናቸው፡፡
ጥራት፣ታማኝነትና ቀጣይነት በሚል መርህ የሚመራው ጣና ፍሎራ ይህንን እውን ማድረግ በመቻሉ በአሁኑ ወቅት በአለም ላይ አበባን በማምረት ከሚታወቁ መሰል ኩባንያዎች ጋር ግንባር ቀደም ተጠቃሽ ኩባንያ እየሆነ መጥቷል፡፡
ኩባንያው ከጊዜ ወደ ጊዜ እያደገ በመምጣቱ በአሁኑ ወቅትም የኢንቨስትመንት እንቅስቃሴውን በማስፋፋት አትክልትና ፍራፍሬ የማምረት ስረ ጀምሯል፡፡ይህንንም በ30 ሄክታር ላይ ፍራፍሬ፣ 25ቱን ሄክታር ደግሞ ለአትክልት ማምረቻ በማዋል በዚህ አመት የዘርፉ የመጀመርያ የሆነውን ምርት ማምረት ችሏል፡፡በቀጣይም በቱሪዝም አገልግሎት ብሎም በሆርቲካልቸርና ተያያዥ ጉዳዮች ዙሪያ የምክር አገልግሎት የስራ ዘርፎች የመሰማራት አላማም አንግቦ በመስራት ላይ የሚገኝ ባለራዕይ ኩባንያ ነው፡፡
ጣና ፍሎራ በተሰማራበት መስክ ለክልላችን ብሎም ለሃገራችን በኢኮኖሚው ዘርፍ በተለይ የውጪ ምንዛሬን በማመንጨቱ ሂደት እያበረከተ ካለው አስተዋጽኦ ባሻገር በስራ እድል ፈጠራውም የበኩሉን እየተወጣ የሚገኝ ኩባንያ ነው፡፡